የአዕምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና እና የማህበራዊ ድጋፍ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለተማሪዎች ተወካይ የሚሰጥ.
1 መግቢያ ይህ ሰነድ የአእምሮ ጤና እና ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ (MHPSS) መሰረታዊ ሀሳቦችን እናያለን፣ በዘመናዊው ማህበረሰብ ውስጥ ያለውን ጠቀሜታ፣ የሚፈታተናቸውን ተግዳሮቶች እና ውጤታማ ትግበራ መንገዶችን በመዳሰስ።የተለያዩ የድጋፍ ዓይነቶችን፣ የማህበረሰቦችን ወሳኝ ሚና እና ደህንነትን ለማሳደግ የፈጠራ ስልቶችን እንመለከታለን። አካላዊ ጤንነት(physical health)- የውስጥና የውጭ የሰውነት ክፍሎች፣ አካላት፣ ሕብረ ሕዋሳትና ሴሎች በተገቢው ሁኔታ ሊሠሩ በሚችሉበት ጊዜ የሚገኝ የደኅንነት ሁኔታ ነው። የአእምሮ ጤና (Mental health) በአዕምሮ ጤናማ መሆን ለሁለንታዊ እድገታችን እና ደህንነታችን እጅግ በጣም አስፈላጊ ነዉ ፡፡በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የአዕምሮ ጤና ጉዳዮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፉ መጥተዋል፣ ድብርት እና ጭንቀት ጋር የሚታገሉ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ እንደ ጦርነቶች፣ወረሽኞች እና የአካዳሚክ ጫናዎች ተባብሰዋል።በመሆኑም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከአዲስ መደበኛ ሁኔታ ጋር መላመድ አለባቸዉ ፡፡ለምሳሌ-ጦርነቶች፣ወቅታዊ ወረሽኞች፣ቴክኖሎጅዎች ወዘተ አዕምሮ ጤና ስሜታዊ፣ ስነ ልቦናዊ እና ማህበራዊ ደህንነታችንን ያጠቃልላል። እንዴት እንደምናስብ፣ እንደምንሰማ እና እንደምንሰራ ይቆጣጠራል። የአእምሮ ጤና ከልጅነት እና ጉርምስና እስከ አዋቂነት ድረስ በሁሉም የህይወት ደረጃዎች ወሳኝ ነው። የስነ ልቦና ማህበራዊ ደህንነትን ለመጠበቅ ወይም ለማሳደግ እና/ወይም የአእምሮ ህመሞችን ለመከላከል ወይም ለማከም ያለሙ የተለያዩ ማህበራዊ እና ስነ ልቦናዊ ጣልቃ ገብነቶችን ያጠቃልላል። ወቅታዊ የነበሩት እና ያሉት ጦርነቶች እንዲሁም የፓለቲካ አለመረጋጋት ስሜታዊና አዕምራዊ ጤና ጉዳዮችን ወደ ከፍተኛ የችግር ዉጤት አስከትሏል፡፡ በመሆኑም ተነሳሽነትን በመቀነሱ ከባድ ፈተና ይፈጥራል፡፡ ስለዚህ በዩኒቨርሲቲዎች ዉስጥ የአዕምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና ድጋፍ መስጠት እና የስነ ልቦና ዝግጁነታቸዉን ማረጋገጥ በጣም አስፈላጊ ነዉ ፡፡.
የአዕምሮ ጤና. [image]. About Mental Health | Mental Health | CDC.
2. ዓላማዎች የስልጠናው አላማ ሰልጣኞች የሚከተሉትን እንዲያደርጉ ማስቻል ነው። 1. ተማሪዎችን በሥነ ልቦናዊ ሁኔታ ለመማር ያላቸዉን እንቅስቃሴዎች መደገፍ በከፍተኛ ፍላጎት እንዲሳተፉ ማስቻል(ለማጥናት፣ከተማሪዎች እና ከዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ ከዉስጥና ከዉጭጋር ጥሩ መስተጋብር እንዲኖር፣ወዘተ) 2. በተለያዩ ችግሮች ምክንያት የሚፈጠሩ የተማሪዎችን የአእምሮ ጤና እና ስነ ልቦናዊ ማህበራዊ ችግሮችን መቀነስ፣ በዩኒቨርሲቲ ዉስጥ ሁለንተናዊ መቀራረብ እንዲኖር ማገዝ/ መንገድ መከፈት ስሜታቸዉን መረዳት 3. ተማሪዎች ስሜታቸውን እና ባህሪያቸውን እንዲያስተዳድሩ መርዳት 4. በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የአእምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና ድጋፍ ክፍሎችን የአሰጣጥ ስርዓታቸዉን ማመቻቸት 5. ለተማሪዎች የአእምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና ድጋፍን እንዴት መስጠት እንደሚቻል አቅጣጫ በማስቀመጥ ለሌሎች ተማሪዎች እንዲያጋሩ በአጠቃላይ ዓላማችን ስለ MHPSS ሁሉን አቀፍ ግንዛቤ መስጠት እና ለአእምሮ ጤንነት/ደህንነት አጠቃላይ አካሄድን መደገፍ ነው። በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ችግሮችን ቀድሞ መከላከል ስራዎችን መስራት፣ችግሮች ካሉ የከፋ ችግር ሳይደርስ ወደ ስነ-ልቦና ክፍል ማምጣት.
3 የሚጠበቀው ውጤት ለተማሪዎች ተወካይ የስነ-ልቦና ዝግጁነት እና ስሜታዊ የእውቀት ልዉዉጥ በየዶራማቸዉ እንዲያደርጉ ማድረግ MHPSS(ሳይኮሎጅስት) ክፍል ማስተዋወቅ ለተማሪዎች እና ለሚመለከታቸዉ ሰራተኞች የMHPSS አገልግሎት መስጠት የሳይኮ-ሶሻል ችግር ያለባቸዉን ተማሪዎች ለመለየት የሚያስችል ልምድ ማጋራት ተማሪዎች የአዕምሮ ጤናቸዉ እና የስነ-ልቦና ጫና ሳይደርስባቸዉ ተመርቀዉ እንዲወጡ ማስቻል.
4. የስነ-ልቦና ዝግጁነት የተማሪ የአእምሮ ዝግጁነት በትምህርት ስኬት ላይ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩ በጣም አስፈላጊ ነገሮች አንዱ ነው። ተማሪዎችን ለመደገፍ በአግባቡ የተዘጋጁ እና የሰለጠኑ ሰራተኞች መኖራቸው አስፈላጊ ነው።በመሆኑም ሰራተኞች ለተማሪ ተወካዮች የስነ-ልቦና ስልጠና በመስጠት ተማሪዎችን ለማገዝ በስነ-ልቦና የተዘጋጁ እንዲሆኑ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የስነ-ልቦና ዝግጁነት ሲባል በዶርምና በብሎክ እንዲሁም በክፍል የሚማሩ ተማሪዎቻችንን በሁለንተናዊ ችግሮቻቸዉ ተጋሪዎች /ተካፋዮች፣ስሜታቸዉን ለመረዳት ቅርብ መሆን፣ለችግሮቻቸዉ መፍትኤ ለማፈላለግ እና የመሳሰሉትን ለመሆን የተዘጋጀን መሆን ያስፈልጋል ማለት ነዉ ፡፡.
የዉይይት ጥያቄ ምን ያህል የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በስነ ልቦና ለመማር ዝግጁ እንደሆኑ ተወያዩ? በዚህ ረገድ ምን ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ? የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ምን ያህል ተማሪዎችን በጭንቀት ለመደገፍ ዝግጁ እንደሆኑ ተወያዩ። በዚህ ረገድ ምን ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ? የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች እና ተማሪዎች የስነ-ልቦና ዝግጁነት ለማሳደግ ምን መደረግ አለበት?.
4.1 የስነ-ልቦና ዝግጁነት ምንድን ነው? የስነ-ልቦና ዝግጁነት እንደሚከተለው ነው- ከላይ እንዳየነዉ ጠቅለል ሲደረግ ለመማር ዝግጁ ከመሆን አንፃር የግለሰብ የአእምሮ ሁኔታ፣ ትምህርትን ተግባራዊ ለማድረግ ትክክለኛ የአዕምሮ ማዕቀፍ መኖር ማለትም የግለሰባዊ ባህሪዎች-እምነት ፣ ችሎታዎች ፣ ፍላጎቶች ፣ ትውስታ ፣ አስተሳሰብ። ትኩረት ፣ የአካዳሚክ የአስተሳሰብ አቅጣጫ ፣ አፈፃፀም። የግለሰቡ ስሜታዊ እና ሥነ ምግባራዊ አቅም ማለት ነዉ ፡፡ 4.2 የስነ ልቦና ዝግጁነት ዓይነቶች 1 የአመለካከት ዝግጁነት(Mindset)- ያለፉትን ልምዶች ወደ አንድ ሁኔታ እንደ ትንበያ መውሰድ፣ ያለፉት ልምዶች ባስከተሉት ሁኔታዎችና ባህሪዎች ላይ በመመስረት የሚደረጉ ንቃተ-ህሊና ግምገማዎች ለምሳሌ በአማራ ክልል የነበሩ(ያሉት) ጦርነቶች ፣አገራዊ ወረሽኞች 2 የማበረታቻ ዝግጁነት(Motivational readiness )- አንድ ሰው የሚያደርገውን ነገር ትርጉም እና ዋጋ ለመገንዘብ እድል/ፍቅር መስጠት 3 የግል ዝግጁነት (Personal readiness )-በተማሪዎች የትምህርት ሂደት ራስን ለመገንዘብ የግል ዝግጁነት.
የአእምሮ ጤና እና ስነ ልቦናዊ ድጋፍ (MHPSS) አስፈላጊነት በእጅጉ በተወሳሰበና እርስ በርስ በተሳሰረ ዓለም ውስጥ የአእምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና ድጋፍ አስፈላጊነት ሊገመት አይችልም።ዘመናዊው ሕይወት ዓለም አቀፍ ወረርሽኞችንና የኢኮኖሚ አለመረጋጋትን እስከ ማኅበራዊ ጫናዎችና የቴክኖሎጂ ከመጠን በላይ ጫናዎችን ጨምሮ በርካታ አስጨናቂ ነገሮችን ያቀርባል።እነዚህ ምክንያቶች በግለሰብ እና በጋራ ደህንነት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ። እየጨመረ የመጣ የአእምሮ ጤና ስጋት ፡- በዓለም አቀፍ ደረጃ የአዕምሮ ጤና ችግሮች እየጨመሩ መምጣታቸው የአዕምሮ ጤና እና ስነ-ልቦና ድጋፍ (MHPSS) ቀድሞ ለመከላከል እና ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመቆጣጠር አስፈላጊ ያደርገዋል። ቀውስ እና የስሜት ቀውስ ምላሽ፡- በአደጋዎች፣ በግጭቶች ወይም በሕዝብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ከተከሰቱ በኋላ፣ MHPSS ግለሰቦች ከጉዳት እንዲያገግሙ እና ሕይወታቸውን እንዲገነቡ ወሳኝ እርዳታ ይሰጣል። የመቋቋም አቅምን ማሳደግ፡- MHPSS ግለሰቦችና ማህበረሰቦች ችግሮችን ለመቋቋም የሚያስችሉ ዘዴዎችን በማዳበርና ህይወትን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመምራት የሚያስችል አጋዥ ሁኔታን በመፍጠር የመቋቋም አቅማቸውን ይገነባል። 4.3 የስነ-ልቦና ዝግጁነት ጥቅሞች፡- የትምህርት አተገባበር ሂደትን ይነካል። የእንቅስቃሴዎችን በተሳካ ሁኔታ ለመቆጣጠር አስተዋጽኦ ያደርጋል። ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች የሚከሰቱ ችግሮች ከሚኖረው የትምህርት ሁኔታ ጋር በቀላሉ እንዲላመዱ ያግዛል።.
4.4 የስነ-ልቦና ዝግጁነት ስልቶች የተማሪዎች የጥናት እና ለዩኒቨርሲቲ ህይወት ዝግጁነት የሚከተሉት ስልቶች አሉት 1 የተነሳሽነት ክፍል 2 አቅጣጫዊ ክፍል 3 የግንዛቤ አሰራር ክፍል 4 ስሜታዊ-ፍቃደኛ ክፍል 4.4.1 የተነሳሽነት ክፍል ይህ አካል ተማሪዎች በአካዳሚክስ ስራ እንዲሳተፉ የአካዳሚክ ፍላጎቶችን እና ምኞቶችን ያካትታል ተማሪዎች ለአካዳሚክስ እንቅስቃሴዎቻቸዉ እና ለዩኒቨርሲቲ ህይወታቸዉ አዎንታዊ አመለካከቶችን እንዲያዳብሩ ያግዛል 4.4.2 አቅጣጫዊ ክፍል የአቅጣጫ ገጽታ ለዩኒቨርሲቲ ህይወት የስነ-ልቦና ዝግጁነት አስፈላጊ ባህሪ ነው የተማሪዎችን የመማር አመለካከቶች፣ መርሆዎች፣ እምነቶች እና በእነሱ መሰረት ለመስራት ዝግጁነትን ያካትታል፡- ዋና አካል የግለሰባዊ እሴት አቅጣጫዎች ፣ የአካዳሚክ እይታ ጥልቀት ነዉ.
4.4.3 የግንዛቤ አሰራር አካል ሁኔታዎችን፣ ክስተቶችን፣ እውነታዎችን የመለየት እና ሊከሰቱ የሚችሉ ውጤቶችን የመተንበይ ችሎታ ነው። ለስኬታማ አካዴሚያዊ እንቅስቃሴ ትኩረትን፣ ግንዛቤን፣ ትውስታን፣ አስተሳሰብን፣ ችሎታዎችን፣ እውቀትን እና ተግባሮችን ያካትታል፡ ዓላማ ያለው የአካዳሚክ ትኩረትን፣ ማስታወስን እና ግንዛቤ መረዳትን ማሳደግ፡ 4.4.4 የስሜታዊ-ፍቃደኝነት አካል ይህ ስልት የተማሪዉን አፈፃፀም ስኬታማ እድገትን እና ዉጤታማነትን የሚያረጋግጡ ስሜት ፣ፍቃደኛ ሂደቶችን ያሳያል ፡፡ይህም የሚከተሉትን ያጠቃልላል ፡- ስሜታዊ ቃና የስሜታዊነት ተነሳሽነት(ትኩረት). ዓላማ ያለዉ መሆን ጽናት ተነሳሽነት ቁርጠኝነት ነፃነት እና ራስን መግዛት.
የቀጠለ… ዓላማ ያለዉ መሆን(ስራዉን በተወሰነ ዓላማ ማስተዳደር) ራስን መግዛት እና ጽናት (ራስን መግዛት እና ዉጤቱን መጠበቅ) ጽናት (ግቡን(ዓላማዉን) ለማሳካት የረጅም ጊዜ ጥረቶች ማድረግ) ተነሳሽነት (ችግሮችን ለመፍታት የፈጠራ ችሎታ እና ፍላጎት መኖር) ቆራጥነት (ወቅታዊ እና ምክንያታዊ ውሳኔ አሰጣጥ እና ንአፈጻጸማቸዉን ማበረታታት) ነፃነት (ከውጫዊ ተጽእኖዎች በተቻለ መጠን መቋቋም) ራስን መተቸት (ስህተቶችን የማስተዋል ችሎታ ፣ የተሳሳቱ ድርጊቶች እና እነሱን ለማስተካከል ፍላጎት መኖር).
የዉይይት ጥያቄ ◆የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስሜታቸውን እና ባህሪያቸውን እንዴት ተረድተው ያስተዳድራሉ? ◆ተማሪዎች የሌሎችን ባህሪ እንዴት ይገነዘባሉ እና ያስተዳድራሉ?.
5 ስሜታዊ ብልህነት(emotional intelligence) ስሜታዊ ብልህነት (EI) ምንድን ነው? ስሜታዊ ብልህነት በማህበራዊ ግንኙነቶች፣ በአካዳሚክ አፈጻጸም እና በአእምሮ እና በአካላዊ ጤንነት እንዲኖር የሚያግዝ ነዉ፡፡ ስሜታዊ ብልህነት በራሳችን እና በሌሎች ሰዎች ስሜትን የመለየት፣ የመረዳት እና የማስተዳደር ችሎታ ነው። ስሜታዊ ብልህነት ሶስት የእውቀት ዘርፎች አሉት 1. ራስን ማወቅ 2. ራስን መምራት 3. በሰዎች መካከል ያለ እውቀት.
5.1 ራስን ማወቅ በስሜታዊነት የማሰብ ችሎታ ያለዉ ለመሆን የመጀመሪያው እርምጃ በራሳችን ውስጥ ስሜቶችን መለየት እና ሌሎች ሰዎችን እንዴት ስሜታቸዉ እንደሚነኩ መረዳት መቻል ነው። ብዙ ሰዎች በሌሎች ላይ የሚያሳድሩትን እውነተኛ ተጽዕኖ አለመረዳት። የራሳችንን ጥንካሬ እና ድክመቶች በአንድ መንገድ(በራስ) ማሰብ እንፈላጋለን ነገር ግን ሌሎች እኛን እንዴት እንደሚገልጹን ብዙ የተለየ ሀሳብ እንዳላቸዉ ማወቅ 5.2 ራስን መምራት በስሜት የማሰብ ችሎታ ያለዉ ለመሆን ሁለተኛው እርምጃ እነዚያን ስሜቶች መለወጥ እና ለእርስዎ ጥቅም ግቦችን ማውጣት ነው። ተማሪዎች እንደተናደዱ ወይም እንደደከሙ እና ደስተኛ እንዳልሆኑ ማወቅ በቂ አይደለም። ስሜትዎን ወደ መረጋጋት ወይም ጉጉት መለወጥ መቻል ጠቃሚ ችሎታ ነው።.
5.3 በሰዎች መካከል ያለ እዉቀት በስሜታዊ ብልህነት የተካነ ለመሆን ሦስተኛው እርምጃ በሌሎች ሰዎች ውስጥ ያሉ ስሜቶችን መለየት እና ማስተዳደር መቻል ነው። በሰዎች መካከል ያለ እዉቀት ሌሎች ሰዎችን ምን እንደሚያነቃቃቸዉ በማወቅ ተፅህኖ ለመፍጠር እና ለማሳመን የሚያስችል ክህሎት (ችሎታ) ነው። እንዴት ስሜታዊ ብልህነትን ማዳበር ይቻላል የበለጠ ስሜታዊ ብልህ ለመሆን የሚከተሉትን ችሎታዎች ማዳበር ያስፈልጋል 1. ስሜቶችን መረዳት 2. ስሜቶችን (መቆጣጠር)ማስተዳደር 3. ስሜቶችን ራስን ለማነሳሳት እና አስተሳሰብን ለማመቻቸት መጠቀም.
5.3.1 ስሜቶችን መረዳት ስሜትን በሚገባ መረዳት የሌሎችን ስሜት መረዳትና ማዘን በተለያዩ ስሜቶች መካከል ያለውን ግንኙነት መረዳት የስሜቶች መንስኤዎችን እና ውጤቶችን መገንዘብ ውስብስብ ስሜቶችን፣ የስሜት ቅልቅሎችን እና እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ ሁኔታዎችን መረዳት በስሜቶች መካከል የሚደረጉ ሽግግሮችን(ለዉጦችን) መረዳት ስሜቶችን ለመረዳት መከተል ያለባቸዉ እርምጃዎች ስሜትን መገንዘብ እና በትክክል መለየት ፡- አካላዊ ፣ስነ-አዕምሮአዊ ወይም ባህሪያዊ ምልክቶችን ጨምሮ ስሜትን መገንዘብ እና በትክክል መለየት መቻል የስሜትን ቀስቃሽ ምክንያቱን ማወቅ ፡- ለዚያ ስሜት ቀስቃሽ የሆነዉን ነገር ማወቅ ያስፈልጋል ዉስጣዊ ወይስ ዉጫዊ ፣እዉነት ወይስ ምናባዊ ነበር የሚለዉን መለየት ከስሜቶች ጋር የተያያዙ ጭብጦችን መተርጎም፡- ከስሜቶች ጋር የተያያዙ ጭብጦችን መተርጎም ስሜቶችን መረዳት ፡-ሁሉንም ስሜቶች በትክክል መረዳት መቻል.
5.3.2 ስሜቶችን መቆጣጠር (ማስተዳደር) ተማሪዎች ከጭንቀት፣ ከፍርሃት፣ ከመጥፎ ስሜት እና ከቁጣ ሙሉ በሙሉ ነፃ አይሆኑም፣ ከሁሉም በላይ ሰው ናቸውና፤ ነገር ግን እነዚህን አስቸጋሪ ስሜቶች ውጤታማ በሆነ መንገድ መቆጣጠር ይችላሉ። እነዚህ (ስሜቶች) ተማሪዎች በሕይወታቸው ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ከማሳካት አያግዳቸውም። 5.3.2.1 የራስን ስሜት መቆጣጠር ደስ የሚያሰኙ እና የማያስደስቱ ስሜቶችን ጨምሮ ለስሜቶች ክፍት መሆን መቻል ስሜቶችን መከታተል እና ማሰላሰል ከስሜታዊ ሁኔታ ጋር መሳተፍ፣ ማቆየት ወይም መለያየት መቻል ማስታወሻ ደብተር ወይም ጆርናል መያዝ የምላሽ ማስተካከያ-ምሳሌዎች እንደ ጥልቅ ትንፋሽ ወይም ማሰላሰል ያሉ የሰውነትን ጸጥ የማድረግ ጣልቃገብነቶችን ያካትታሉ.
5.3.2.2 የሌሎችን ስሜት መቆጣጠር ተማሪዎች ሌሎችን ለማነሳሳት እና ለማረጋጋት ማህበራዊ ክህሎቶች ሊኖራቸው ይገባል፥ በሚከተሉት መንገዶች: ሁሉንም የመገናኛ ምክንያቶች እና አውዶች መፈለግ ማዳመጥ እና መተሳሰብ ከሌላው ሰው ጋር ያላቸውን ግንኙነት መመስረት እና ማረጋገጥ ስለሚያስፈልጋቸው ነገር ምክራቸውን መጠየቅ ተገቢ ከሆነ፣ ንክኪ ወይም አካላዊ ፍቅርን መጠቀም የዓይን ግንኙነትን መጠበቅ፣ ታጋሽ መሆን እና ለሌላው ሰው ቀስ ብሎ ጊዜ መስጠት የተናደደው ሰው እንደተሰማ ማሳወቅ እና መብቱ/መብቷ ሊከበር እንደሚገባው መንገር ለተፈጠረው ነገር ይቅርታ መጠየቅ: የግድ ኃላፊነትን መውሰድ ሳይሆን ለተፈጠረው ነገር ርህራሄን መግለጽ ተመሳሳይ ግቦች እንዳላችሁ ማረጋገጥ የተገነዘቡትን ስጋት መረዳት እና በሂደቱ ውስጥ የት እንደሚደርሱ ማወቅ.
5.3.3 ራስን ለማነሳሳት ስሜቶችን መጠቀም ተማሪዎች በሕይወታቸው ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ለማድረግ መነሳሳት አለባቸው። የመነሳሳታቸው ሁኔታ በሚቀንስበት ጊዜም እንኳ የሚከተሉትን በማድረግ ራስን የመግዛት ችሎታ ማዳበር ይቻላል: ከተያያዥ ስሜቶች መሠረት በማድረግ ሐሳብን ማስተካከል እና ቅድሚያ መስጠት እንዲሁም ፍርድን እና ትውስታን ለማመቻቸት ስሜቶችን ተቆጣጥሮ ቅድሚያ ለሚሰጠዉ መስጠት ጎልተዉ የወጡ የስሜት ለዉጦችን በተለያየ እይታ ማየት ችግር መፍታትን እና የፈጠራ ችሎታን ለማመቻቸት ስሜታዊ ሁኔታዎችን መጠቀም.
አሁን ባለንበት የትምህርት አዉድ ዉስጥ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምንምን የስነ-አዕምሮ ፣የስነ-ልቦና እና ማህበራዊ ችግሮች ያጋጥማቸዋል.
6 የአዕምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና እና ማህበራዊ ደጋፍ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የአእምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና እና ማህበራዊ ችግሮች የተለያዩ ችግሮች ማለትም ወረርሽኝ፣ጦርነት፣ያልተየግል በተማሪዎች ላይ ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ የአእምሮ ጤና እና ስነ-አእምሮአዊ ጫና ፈጥሯል። 6.1 ተማሪዎች ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ ችግሮች፦ የዕለት ተዕለት ተግባራት መቋረጥ የመነሳሳት ስሜት መቀነስ እና ለጥናት ፍላጎት ማጣት ከትምህርት ገበታ መውጣት (Dropout) ድብርት (Depression) ጭንቀት፣ ስጋት፣ ውጥረት፣ ለጦርነቱ ፍርሃት ከአሰቃቂ ሁኔታ በኋላ የሚከሰት የጭንቀት መታወክ (በተለያዩ ክስተቶች የከፋ ነገር ማየት) የሴት ልጅ ጋብቻ፣ የቤት ውስጥ ብጥብጥ፣ የእኩዮች መስተጋብር ማጣት አደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚ መሆን የራስን ሕይወት የማጥፋት ሀሳብ እና ሙከራ ማድረግ በተለያየ ምክንያት ከእኩዮቻቸዉ ጋር ግንኙነት መቆም እና የገለልተኛነት ስሜት መሰማት በወቅታዊ ጦርነቶች ወቅት የሚወዱትን ቤተሰብ/ሌላ ሰዎችን በማጣት ምክንያት ጥልቅ ሀዘን ዉስጥ መግባት.
6.2 ተማሪዎች የአዕምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና ድጋፍ ማድረግ MHPSS መስጠት ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ደህንነት ጥበቃ ማድረግ የተማሪ ተወካዮች የእያንዳንዱን ተማሪ እንቅስቃሴ መከታተልና በቅርበት ፍቅር በመስጠት ችግራቸዉን መጋራት የተማሪዎች ተወካይ ማህበራዊ እና ስሜታዊ ድጋፍ ለተማሪዎች በቅርበት ማሳተፍ፣ ተማሪዎች ከሰራተኞች ጋር እንዲቀራረቡ መደገፍ፣ ግንኙነቶችን መልሶ ለመገንባት እና ለአካዳሚክ ትምህርት መሰረት ለመፍጠር ወሳኝ ነው። የተማሪዎች ተወካይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የገጠማቸዉን ችግሮች ለመፍታት ወደ ባለሙያዎች እንዲመጡ ማድረግ 6.3 ሰራተኞች የአእምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና ድጋፍ ... ዩኒቨርሲቲዎች የሰራተኞችን ደህንነት በጥንቃቄ ማቀድ አለባቸዉ ፡፡ ይህም የሚከተሉትን ለማድረግ እንዲችሉ ያግዛል ፡- የተማሪዎቻቸውን ማህበራዊ እና ስሜታዊ ደህንነት እና የመማር ፍላጎቶችን መደገፍ ። በበተለያዩ ችግሮች ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ እና ዉጭ ለሚኖሩ ችግሮች በሰራተኞች እና በተማሪዎች ሊደርሱ የሚችሉ የስሜት ቀዉሶችን ቀድሞ መለየት እና መዘጋጀት የሰራተኞቹን ጥንካሬዎች ማወቅ እና ማጎልበት.
7 የአገልግሎት ዓይነቶች ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎችን አካዳሚያዊ፣የባህሪ እና ማህበራዊ -ስሜታዊ ፍላጎቶችን በዩኒቨርሲቲዉ አካባቢ ዉስጥም ሆነ ዉጭ ለመፍታት ስልታዊ እና አጠቃላይ አቀራረብ ማዘጋጀት አለባቸዉ ፡፡ እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ:- የአካዳሚክ ድጋፍ የአእምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና ድጋፍ 7.1 የአካዳሚክ ድጋፍ የተማሪዎች ምክር አገልግሎት የበለጠ ተደራሽነቱን በማስፋት መቀጠል እና ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም አገልግሎት መስጠት ለተማሪዎች በሚመች ሰዓት አገልግሎት መስጠት እና በአጠናን ዘዴዎች በግልና በቡድን ማማከር የአካዳሚክ ዉጤታቸዉ ጥሩ እንዲሆን መገዝ ከመምህራን ጋር ያላቸዉን ግንኙነት ጥሩ እንዲሆን ድጋፍ ማድረግ እና በእቅድ እንዲመሩ ድጋፍ ማድረግ 7.2 የአእምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና ድጋፍ ምንም ዓይነት የተዳከመ ምልክት ሳይታይባቸዉ በጦርነት እና በአካዳሚያዊ ምክንያት ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት እንዳይሰማቸዉ እና መቋቋም እንዲችሉ ስልጠና መስጠት በከፍጠኛ ጭንቀት ዉስጥ ላሉ ተማሪዎች ድጋፍ እና ክትትል ማድረግ ድጋፎች የአካዳሚያዊ ጊዚያቸዉን እንዳይነካ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ድጋፍ ማድረግ ከሰዎች ጋር ያላቸዉን ግንኙነት በጥሩ ሁኔታ እንዲያስኬዱ ማገዝ (በተለይም በትርፍ ጊዚያቸዉ ከሰዎች ጋር እንዲዝናኑ ).
8 የአዕምሮ ጤና እና ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ መቼ ሊሰጥ ይችላል በተለያዩ ችግሮች ላይ ያሉ የስነ-ልቦና ድጋፍ ያስፈልጋል ። በችግሮች የመጀመሪያ ደረጃዎች ውስጥ ፣ አስቀድሞ የሚጠበቀው ጭንቀት እና ጭንቀት ከፍተኛ ሊሆን በሚችልበት ጊዜ። ችግሮች ከፍተኛ ደረጃዎች ሲደርሱ በተለይም ሰዎች ለአሰቃቂ ሁኔታዎች የተጋለጡበት የአዕምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና ድጋፍ ሲያስፈልግ ... 9 ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ድጋፍ ወሳኝ የሚሆንባቸው ሶስት ጊዜዎች አሉ፡- ተማሪዎችን ወደ ካምፓስ እንዲገቡ በሚደረግበት ወቅት የሚሰጥ ድጋፍ (በአካል ወይም በሌሎች አማራጮች) ተማሪዎች ግቢ ከገቡ በኋላ በተለያዩ ችግሮች እንዳይጨናነቁ ድጋፍና ክትትል ማድረግ በአጠቃላይ ተማሪዎችን ከግቢ ለቀው(ተመርቀዉ) እንዲወጡ በሚደረግበት ወቅት ችግሮችን መቋቋም የሚችሉ የራስ መተማመን እና የስነ-ልቦና ጥንካሬ ተላብሰዉ እንዲወጡ ማድረግ.
10 ተማሪዎችን ወደ ትምህርታቸዉ ብቻ እንዲያተኩሩ ለማዘጋጀት ፡- ለአካዳሚክ ትምህርት እና ለካምፓሱ ህይወት የተማሪዎችን የስነ-ልቦና ዝግጅት እንዲያደርጉ ማገዝ ተማሪዎች መርጃዎችን እና ድጋፎችን የሚያገኙበት ቦታዎችን/ሁኔታዎችን ማዘጋጀት ለተማሪዎች ድጋፍ (የተማሪ ዲኖች፣ የተማሪ ማዕከላት፣ የኮሌጅ ዲኖች ክፍል ኃላፊዎች፣ ፋኩልቲ ወዘተ.) ሁሉም ተማሪዎች ያሉበትን ቦታ እንዲያዉቁ ማገዝ በሁሉም ዘርፎች መረጃ ወጥነት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ ለተለያዩ የተማሪዎች የቡድን ግንኙነቶችን ማበጀት(ለምሳሌ፡- የእናንተ ዉክልና) ተማሪዎች ወደ ትምህርታቸዉ እንዲያተኩሩ የሚያግዙ መረጃዎችን በቀላሉ ተደራሽ መሆኑን በማረጋገጥ በሰፊው ማጋራት። የተለያዩ የተፈጥሮና ሰዉ ሰራሽ ችግሮች ሲያጋጥሙ በፍጥነት የመፍትሄ አማራጮች ላይ ብቻ አተኩሮ መስራት ከዉጫዊ ተፅህኖዎች ነፃ እንዲሆኑ ማገዝ(ለመጡበት ዓላማ ብቻ እራሳቸዉንና ጊዚያቸዉን መሰዋት እንዲያደርጉ ማገዝ) ሁሉም ባለድርሻ አካል በቅርበት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ የወጣ ባህሪ ያለዉ ተማሪ ሲያጋጥም መምከር፣እንዲመከር ማገዝ/ማመቻቸት.
11 ጭንቀትን መቆጣጠር በተለያዩ ችግሮች ወቅት ተማሪዎች ውጥረትን እንዴት መቋቋም ይችላሉ፡- በማህበራዊ፣ አእምሯዊ ስሜታዊ እና አካላዊ እራስን እና ሌሎችን በእንክብካቤ በመያዝ የሚከተሉትን ምክሮች ጭንቀትን እንድንቆጣጠር ያግዙናል ፡- ደህንነትን እንዴት መጠበቅ እንዳለብዎ ይወቁ ነገሮችን በአግባቡ ይመልከቱ(ነገሮችን መመዘን መቻል) ጤናማ ይሁኑ ችግሮችን የመቋቋ አቅም ይገንቡ እቅድ ይኑራችሁ(በእቅድ መመራት) መልካም ግንኙነትዎን ማስቀጠል እርዳታ መቼ እንደሚፈልጉ ማወቅ እርዳታ የት እንደሚያገኙ ማወቅ(ችግሩ የከፋ ደረጃ ሳይደርስ ለማማከር) መረጃዎችን ከታማኝ ምንጭ ማግኘት(ያልተረጋገጡ ወሬዎችን መጠንቀቅ) ፍርሃትን የሚቀሰቅስ ድህረ-ገፆችን አለመጠቀም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የችንቀት ምንጮችን ማወቅ እና መፍትሄዉ ላይ ማተኮርና ተግባራዊ ማድረግ በራስ ዕቅድ መመራት(በሌሎች ተፅህኖ አለመዉደቅ) ትክክለኛ የአመጋገብ ዘዴን መጠቀም እና በቂ እረፍት ማድረግ ከአልኮል መጠጥ ነፃ መሆን የግል ንፅህና መጠበቅ ሰዎችን መርዳት.
ነገሮችን በትክክል መመልከት(እዉነታዎችን አምኖ መቀበል) ለዘመናት ሰዎች ችግሮችን ተቋቁመዉ ኖረዋል አብዛኛዉ ሰዉ የመቋቋም አቅም አለዉ፣ አብዛኛዉ ሰዉ ችግሮችን ተቋቁሞ ያሰበዉ ደረጃ ላይ ይደርሳል/ከወደቀም ይነሳል ተማሪዎች በከፋ ሁኔታ ላይ(በመጥፎ እሳቤዎች) ላይ እንዳያተኩሩ እዉነትን ማሳየት ነገሮች የተሻለ እንደሚሆኑ ተማሪዎች እንዲያስታውሱ መርዳት አሁን ያለንበት ሁነት እንደሚቀየር/እንደሚለወጥ ማመን እና መሻት ያላንዳች ፈተና ስኬት ሊመጣ እንደማይችል መረዳት እና ፈተናዎችን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ፈተናን ማለፍ እና የበለጠ ጠንክሮ መዉጣት ሁሌም ቢሆን አዕምሮን መልካም ሀሳብ መመገብ ያስፈልጋል ፡፡ ምክንያቱም ሙሉ ዉሎ አዳራችን አምሮን በመገብነዉ ልክ ስለሆነ ዉለን የምናድረዉ.
11.1 የአስተሳሰብ ለዉጦች፡- ጊዚያዊ ግራ መጋባት ትኩረት አለማድረግ የችግር አፈታት አቅም መቀነስ ስሜትን ለራስ ብቻ መያዝ ያሳለፍትን ችግር እየደጋገሙ ማሰብ ቅዥት ተስፋ መቁረጥ ራስን የማጥፋት ሀሳቦች ሌሎችን የመጉዳት ሀሳቦች 11.2 የስሜታዊ ለዉጦች፡- ፍርሃት ሀዘን መበሳጨት ደስታ ማጣት ጭንቀት ድብርት ከአሰቃቂ ሁኔታ በኋላ የሚከሰት የጭንቀት መታወክ.
11.3 የባህሪ ለዉጦች፡- በቀላሉ መደናገጥ የእንቅልፍ መዛባት የምግብ ፍላጎት አለመኖር ብቸኝነት የአልኮል ተጠቃሚ መሆን አደጋ ላይ የሚጥሉ ተግባራትን መከወን ያለ ሀኪም እርዳታ እራስን ማከም/ያልታዘዘ መድሀኒት መዉሰድ የሀሳብ ጠበብትኝነት መነጫነጭ/የባህሪ መለዋወጥ 11.4 የመንፈሳዊ ለዉጦች፡- እምነትን መጠራጠር የፈጣሪን ድርጊት መጠራጠር ከእምነት ጋር የተያያዙ ተግባራትን ማቆም እምነትን በሌሎች ላይ ለመጫን መሞከር.
12 የአዕምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና እና የማህበራዊ ድጋፍ በክፍሉ እና በተማሪዎች ተወካዮች ዉስጥ መግባባት የሚያስፈልጉ ነጥቦች(በጋራ የሚከናወኑ ተግባራት) 1 በዩኒቨርሲቲዉ ዉስጥ የአዕምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና እና የማህበራዊ ድጋፍ ሰጭ ቢሮዎች ክፍሉ የድጋፍና የክትትል ስራዎችን ለመስጠት መዘጋጀት እና በቢሮ መገኝት ቢሮዎችን የማስተዋወቅ ስራ መስራት ከተማሪዎች ተወካይ ጋር የግንኙነት መንገዶችን ማመቻቸት ልዩ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎችን ድጋፍና ክትትል ማድረግ ተከታታይነት ያለዉ ስልጠና ማመቻቸት 2 በተማሪ ተወካዮች ልዩ ፍላጎት ያላቸዉን እና ከዚህ በፊት የአዕምሮ ጤና ችግር ያለባቸዉን ተማሪዎች አጣርቶ ማምጣት ለተማሪዎች ስለ ክፍሉ ማስተዋወቅ እና ቢሮዉ ያለበትን ቦታ ማሳየት ከእያንዳንዱ ተማሪ ጋር ያላችሁ ግንኙነት ከሰፋባችሁ ችሁ ሌላ ሊያግዛችሁ የሚችል መንገድ በመጠቀም የተማሪዎችን የአዕምሮ ጤና እና የሳይኮ-ሶሻል ችግሮችን ለመቀነስ ማገዝ መረጃዎችን ለክፍሉ ባለሙያዎች በወቅቱ ማድረስ እና ችግራቸዉን መጋራት/ መቀነስ 3 በተቻለ መጠን የስልክ የመረጃ ልዉዉጦችን መጠቀም ለድንገተኛ የአዕምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና እና የማህበራዊ ምክሮችን ማመቻቸት ራስን የማጥፋት ሀሳቦችን እና ሌሎች የግል ጉዳዮችን ለመፍታት የስልክ የምክርን ድጋፍ መስጠት.
4 ከዚህ በፊት የአዕምሮ ጤና ችግር ያለባቸዉ ተማሪዎች በመለየት ተጨማሪ ድጋፎችን ማድረግ የአዕምሮ ጤና ክትትልና መድሐኒት የሚወስዱ ተማሪዎች ተለይተዉ ክትትልና ድጋፍ መደረግ አለበት ከዚህ የከፋ ከሆነ ከሚመለከተዉ አካላት ጋር በመሆን የተሻለ መፍትሄ በማስቀመጥ የተማሪዉን ደህንነት መጠበቅ 5 ተማሪዎች ከቤተሰቦቻቸዉ ጋር ያላቸዉን ግንኙነት እንዲያዳብሩ ማገዝ 6 ተማሪዎች ከሌሎች ተማሪዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖራቸዉ ማገዝ 7 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲዎችን ህግና ደንብ እንዲጠብቁ በማድረግ ከጭንቀት መከላከል 8 በጎ ስራዎች ስራዎች ላይ መሳተፍ ፡-የአዕምሮ ዕርካታ በማግኘት የበለጠ ዉጤታማ እንድንሆን ስለሚያግዝ 9 ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸዉ የጤና ዕቅድ እንዲኖራቸዉ ማገዝ፡- የአካላዊ ጤና እንዲጠብቁ ማገዝ የመንፈሳዊ እንቅስቃሴ(የፀሎት) ጊዜ እንዲኖራቸዉ ማገዝ የመዝናኛ ጊዜ እንዲኖራቸዉ ማገዝ ማህበራዊ ግንኙነት እንዲኖራቸዉ ማገዝ.
አመሰግናለሁ !!! የትምህርት ዓመቱን በደስታና በስኬት እንዲያልቅ እመኛለሁ !!!.